Fana: At a Speed of Life!

በኢኮኖሚና ፖለቲካል ዲፕሎማሲ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ አፈፃፀም መታየቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በኢኮኖሚና ፖለቲካል ዲፕሎማሲ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ አፈፃፀም መታየቱን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው በዚህ ግምገማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ100 ቀን ዕቅድ ትግበራ ላይ ግምገማ ተካሄዷል።
በፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ፣ በፕላን ስታቲስቲክስ እና ፖሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ እና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ በወይዘሮ ጥሩማር አባተ የተመራው ይኸው ግምገማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተወካዮችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፈተናው ብዙ ቢሆንም ወዳጅ ሀገራትን በማጠናከር፣ በተለይ ዳያስፖራው በጣም የሚያኮራ ስራ መስራቱን ጠቅሰው ይህን አንድነት ማስጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።
በዚሁ ግምገማ ዶክተር ፍጹም በኢኮኖሚና ፖለቲካል ዲፕሎማሲ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ አፈፃፀም መታየቱን አንስተዋል፡፡
አያይዘውም በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ የሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር አጋሮችን ማበራከት፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ፣ የጎብኚዎችን ፍሰት መጨመር ላይ መልካም አፈፃፀም እየታየ እንደሚገኝም መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.