Fana: At a Speed of Life!

በ4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የአራት የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ውል ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለ4 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ የ4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ውል ስምምነት ከተለያዩ ተቋራጮች ጋር ተፈራረመ።

በውል ስምምነቱ ላይ የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም መንገድ ከሚገነባባቸው አካባቢዎች የተወከሉ የሃገር የሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

የመንገድ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል።

የሚገነቡት መንገዶችም የቆሼ – ሚጦ – ወራቤ፣ ጋምቤላ – አቦቦ – ጎግ – ዲማ፣ የግሸን መገንጠያ እና የጎንጂ – ቆለላ መሆናቸው ተገልጿል።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ1 አመት እስከ 3 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ሁሉም መንገዶች በአስፋልት ደረጃ የሚገነቡ ሲሆን አጠቃላይ ርዝመታቸውም 169 ኪሎ ሜትር መሆኑን የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል።

የመንገዶቹ ግንባታ ለመኪኖች ደህንነት ከሚኖረው ፋይዳ ባሻገር ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረውን ጊዜ በማሳጠር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

በቅድስት ተስፋዬ እና ማርታ ጌታቸው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.