Fana: At a Speed of Life!

የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገላት ቫዮሊን የተጫወተችው ሴት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እንግሊዛዊቷ ሴት ውስብስብ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገላት የምትወደውን ቫዮሊን መጫወቷ አነጋጋሪ ሆኗል።

የ53 አመቷ ተርነር በቀኝ የጭንቅላቷ ክፍል ያለውን ዕጢ ለማስወገድ የግድ ከባዱን የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ማድረግ ነበረባት።

ችግሩ ግን በህክምና ሂደት የሚፈጠር አንድ ስህተት ተርነርን ከቫዮሊን እስከወዲያኛው ያለያያታል።

ይህ እንዳይሆን ደግሞ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልግ ነበርና የቀዶ ጥገና ባለሙያዎቹ አንድ መላ ዘየዱ፤ የሰመመን መርፌ ከወጓት በኋላ ጭንቅላቷን ይከፍታሉ።

ይህ ከተሳካ እና ለህክምናው የሚያስፈልገውን ካሟሉ በኋላ ከሰመመኗ እንድትነቃ በማድረግ የምትወደውን ቫዮሊን እየተጫወተች ቀዶ ጥገናውን በጥንቃቄ አከናውነዋል።

ይህ የሆነው ደግሞ በህክምና ሂደት የምትፈጠር አዲት ስህተት ተርነርን ቫዮሊን እንዳትጫወት ሊያደርጋት ስለሚችል ነው ብለዋል የህክምና ባለሙያዎቹ።

በቀዶ ጥገና የወጣላት ዕጢ ቋንቋንና የግራ እጅ እንቅስቃሴን  የሚቆጣጠር እንደነበርም ነው የተገለጸው።

ተርነር ከቀዶ ጥገናው ሶስት ቀናት በኋላ ከሆስፒታል መውጣቷም ተነግሯል።

ምንጭ፦ ግሎባል ኒውስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.