Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ18 ሺህ በላይ ጥይትና ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ እና ከሳንጃ ወደ ጎንደር ሊገባ የነበረ ከ18 ሺህ በላይ ጥይትና ሽጉጦች መያዙን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኮማንደር ውብነህ አስናቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በሁለት ባለሾስት እግር ተሸከርካሪዎች ውስጥ 76 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፣ 18 ሺህ 200 የሽጉጥ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

በተጨማሪም 518 የብሬን ጥይት ከሳንጃ ወደ ጎንደር ሊገባ ሲል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አይነት ውሃ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኢትዮጵያ ካርታ በተባለ ቦታ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡

ከወንጀሉ ጋር የተጠረጠረ የባጃጅ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፥ ሌላኛውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያያደረገ መሆኑም ተገልጿል ።

የኬላ ፍተሻው ተጠናክሮ እየተሰራ ነው ያሉት ኮማንደር ውብነህ፥ ህብረተሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰላም አስመላሽ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.