Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈፀሟቸው አረመኔያዊ ድርጊቶች እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች በአማራ ክልል ግድያና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የፈፀሟቸው አረመኔያዊ ድርጊቶች አሳስቦኛል ስትል አሜሪካ ገለፀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን መሰረት አድርጎ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም፥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት የህወሓት ታጣቂዎች በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ አካባቢ በአማራ ክልል አረመኔያዊ ድርጊት መፈጸማቸውን ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም እየተፈፀሙ ያሉት የጭካኔ ድርጊቶች ለወታደራዊ ግጭቱ በፍጥነት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ የሚያመላክቱ ናቸው ብሏል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፡፡

ስለሆነም ሁሉም ወገኖች በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እና በንጹሀን ላይ የሚደርሰው ግፍ እንዲቆም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ፤ ግጭቱን ለማስቆም እና ፍትህን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን መሆኑን አስታውቋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.