Fana: At a Speed of Life!

በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ሰራተኞችን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ሰራተኞችን የመከላከያ ማስረጃ ለመጠባበቅ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለከሳሾቹ ከዚህ በፊት ፈቅዶላቸው የነበረው የ30 ሺህ ብር ዋስትና መብት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 16 /2014 ዓ/ም በጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተሽሮ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ መወሰኑ ይታወሳል።

ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን የተቋሙ የፀረ ሽብር ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 20 ተከሳሾች በችሎቱ ተገኝተዋል።

ችሎቱ ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር ማስረጃ ውጤት ለመጠባበቅ ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም፥ የተከሳሽ ጠበቆች መዝገቡ ይግባኝ ላይ ስለነበረ ማስረጃውን አለማቅረባቸውን ለችሎቱ አስረድተው አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በዚሁ መዝገብ አንድ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይፈልግ ለችሎቱ በመግለጹ ችሎቱም ሌሎች በተመሳሳይ ሃሳብ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ የማይፈልግ ተከሳሽ ካለ በፅሁፍም በቃልም ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የመከላከያ ማስረጃ ውጤት ለመጠባበቅ ለየካቲት 25 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከፍትህ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.