Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀን በዱባይ ኤክስፖ 2020 ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀን በዱባይ ኤክስፖ 2020 ተከበረ፡፡

በመርሃ ግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የዱባይ ኤክስፖ 2020 ከፍተኛ አመራሮቸና ከተለያዩ የአረብ ኢሚሬቶች ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን እና የሌሎች ሃገራት ተሳታፊዎችም ፕሮግራሙን ታድመዋል።

በኤክስፖው የትርዒት ማሳያ ስፍራ አልዋስል እየተካሄደ ባለው ዝግጅት ኢትዮጵያ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጋር ያላት ጠንካራ ግንኙነትና በኤክስፖ የኢትዮጵያ እልፍኝ ለጎብኚዎች የተቀመጡ የባህል፣ የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ማሳያዎች ኢትዮጵያ ያላትን ሃብት በማስተዋወቅ ትልቅ እድል የሰጠ መሆኑን አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገልፀዋል፡፡

ለዚህም የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለሚያደርጉት ድጋፍ እና እድል ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ግንኙነት ከነብዩ መሃመድ ጀምሮ ዘመናትን የተሻገረና አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ያነሱት አፈጉባኤው ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በዜጋ ተኮር እና ሌሎች የልማት ስራዎች ላይ ተቀራርበው ለመስራት በመሪዎች ደረጃ የተፈረሙ ስምምነቶችን አስታውሰዋል።

የዓድዋ የድል በአል ትርጉምና ያስገኘውን ትሩፋት በማስታወስም በዓሉ የሁላችንም ነው ብለዋል።

በመድረኩ የብሄራዊ ቴአትር የባህል ውዝዋዜ ቡድን የዐድዋን ድል የሚያሳዩ ትዕይንቶችንና ውዝዋዜዎችን አቅርበዋል።

በፍሬህይዎት ሰፊው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.