Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሰላም ግንባታ ላይ ለሚያከናውነው ተግባር ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስተርሊንግ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዙሪያ ለሚያከናውነው ተግባር የሚውል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እ.አ.አ በ2022/23 በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ሊሰራው ያሰበውን የሰላም ግንባታ፣ የግጭት አፈታትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር የበጀት ድጋፍ እንደተደረገለት የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ጉባዔው የበጀት ድጋፉን ያገኘው መቀመጫውን በአሜሪካ ዩታ ግዛት ካደረገው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ነው የገለጹት።
ጉባዔው ዕቅዱን ለመፈጸም የሀብት ማፈላለጊያ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ለፋውንዴሽኑ የላከ ሲሆን÷ ፋውንዴሽኑም ፕሮጀክቱን በመቀበል፣ የበጀት ድጋፍ ለማድረግ ፈቅዷል ነው ያሉት።
በዚህም መሠረት ጉባዔውና ፋውንዴሽኑ የድጋፍ ስምምነት ፊርማ ዛሬ በአሜሪካ ዮታ ግዛት አከናውነናል ብለዋል።
ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊትም ለጉባዔው ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረጉን አስታውሰው÷ በቅርቡም ለጉባዔው ተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.