ሩስያ ህልውናዋ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች – የክሬምሊን ቃል አቀባይ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሩሲያ ህልውናዋ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናገሩ፡፡
ቃል አቀባዩ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ “ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሊጠቀሙ ይችላሉ ወይ ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት መልስ፥ ሩስያ የሀገር ውስጥ ደህንነት ፖሊሲ ያላት ሀገር መሆኗን ገልጸው ደህንነቷ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ ልታውል ትችላለች ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ በሀገሪቱ የደህንነት ፖሊሲ መሰረት ሩስያ የኒውክሌር አማራጭ ልትጠቀም የምትችልበት ምክንያት አለመኖሩን ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡
በዩክሬን እየተካሄደ ያለውዘመቻ በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑንም ነው ቃል አቀባዩ የጠቀሱት።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፥ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የኬሚካል እና ባዮሎጂካል መሳሪያዎችን ለመጠቀም እያሰበች እንደሆነ ግልፅ ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህን የሚያደርጉ ከሆነ ምዕራባውያን እና አሜሪካ የአፀፋ ምለሽ ይሰጣሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረ ከሦስት ቀናት በኋለ የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱን የኑክሌር መከላከያ ኃይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፕሬስ ቴቪ በዘገባው አስታውሷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!