Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ለቅድመ ዝግጅት ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቅድመ ዝግጅት የአማራ ክልል ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቋል፡፡
ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ እንዳስታወቀው÷ 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በባህርዳር ከተማ እንዲካሄድ ውሳኔ በማሳለፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡
ነገር ግን የካቲት 21 ቀን 2014ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስበሰባ አንዳንድ ክለቦች እና ክልሎች ያቀረቡትን የበጀት ወጪ መጠንን ቁሳቁስ ለማጓጓዝ የሚፈጀውን ርቀት ታሳቢ በማድረግ ውድድሩ በሐዋሳ እንዲካሄድ መወሰኑ ተመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ ጠቅላላ ጉባኤው ቀደም ሲል የወሰነውን ውሳኔ ባለማክበሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን እና የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮን ይቅርታ ጠይቋል፡፡
በመሆኑም ክልሉ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ ያወጣቸው ወጪዎች በተገቢው መንገድ ተጣርተው በፌዴሬሽኑ የሚሸፈኑ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፃፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.