Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ ተብሎ መመረጡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል ፋይናንስ ለ29ኛ ጊዜ በፈረንጆቹ 2021 ዓመታዊ የዓለም እና የየአገራቱን ምርጥ ባንኮች ምርጫ ይፋ አድርጓል።
 
በዚህም መሰረት ከአፍሪካ አህጉር የደቡብ አፍሪካው “የስታንዳርድ ባንክ” አንደኛ ምርጥ ባንክ ተብሎ ሲሰየም÷ከኢትዮጵያ ደግሞ አዋሽ ባንክ ተመርጧል።
 
ምርጫው የተካሄደው በ150 አገራት ላይ ባሉ ባንኮች መካከል ሲሆን÷ 36ቱ ባንኮች ከአፍሪካ የተመረጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ÷ ባንኩ ከ36ቱ ባንኮች ውስጥ መካተት የቻለው ባሳለፈው በጀት ዓመት የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ዓሉታዊ ተፅዕኖ፣የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት የመሳሰሉ ፈተናዎችን ተቋቁሞ እጅግ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡
 
ባንኩ በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ላይ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ሂሳብ ኤልሲ ማርጂንን ጨምሮ 107 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መድረሱን ጠቁመዋል፡፡
 
ይህ የተቀማጭ ሂሳብ መጠን በአዋሽ ባንክ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በግል ባንኮች ታሪክ የመጀመሪያው በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ መቻሉን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።
 
የ2021 የባንኩ ያልተጣራ ትርፍ 5 ነጥነብ 58 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን ÷ይህም ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1 ነጥብ 39 ቢሊየን ብር ወይም የ33 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡ ተነግሯል።
 
በማህሌት ተክለብርሃን
 
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.