የለሙ ቴክኖሎጂዎችና የተሰበሰቡ የሳተላይት መረጃዎች ተግባር ሊውሉ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
በሳተላይት መረጃ መቀበያና መቆጣጠሪያ ጣቢያ የሚሰበሰቡት መረጃዎች ለሚፈለገው ተግባር እንዲውሉ የማስታወቂያና የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት በትኩረት መከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ÷ የማስተዋወቅ ተግባራትን ለማከናወን አዲስ እስትራቴጂ ተቀርጾ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ግብረ ኃይል በማቋቋም ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወቅቱ ከሚያመጣቸው ፈተናዎች አሸንፋ እንድትወጣና በቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንድትሆን ዘርፉን በቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል ማጠናከር እንደሚገባ መጠቆሙን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡