Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሀሰን ታጁ ከኩዌት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሀሰን ታጁ ከኩዌት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አምባሳደር ሱለይማን አሊ ሰዒድ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ሀሰን ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ሁለትዮሽ ግንነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተለይም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በሚፈጥሩ የሠራተኛ ስምሪት ስምምነቶች እንደዚሁም ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በባህልና በሌሎች መስኮች ትብብራቸውን ይበልጥ በሚያሳድጉበት ሁኔታ ላይ መመምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.