Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የጦር መሳሪያ አመታዊ ግብይት ከ2 ትሪሊየን ዶላር አለፈ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ሃገራት ወታደራዊ ሀይል ለመገንባት የሚያወጡት አመታዊ የጦር መሳሪያ ግብይት በፈረንጆቹ 2021 አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲቲዩት ባወጣው ሪፖርት ዓለም ላይ ለወታደራዊ ግንባታ 2 ነጥብ 113 ትሪሊየን ዶላር ወጪ መሆኑን አመላክቷል።
ከዚህ ውስጥ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ እንግሊዝ እና ሩሲያ 62 በመቶውን ይሸፍናሉ ነው የተባለው፡፡
እንደ ኢንስቲቲዩቱ ገለፃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጫና ቢፈጠርም በ2021 ዓለም ለወታደራዊ ግንባታ ፈሰስ ያደረገችው ገንዘብ ለሰባተኛ ጊዜ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል፡፡
አሜሪካ 801 ቢሊየን ዶላር ወጪ ስታደርግ ቀደም ካለው አመት አንጻር ቅናሽ ቢያሳይም ከፈረንጆቹ 2012 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ ግን 24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።
ቻይና 293 ቢሊየን ዶላር በማውጣት ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ህንድ 76 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጋለች።
ከዚህ ውስጥ 64 በመቶው ገንዘብ ከሃገር ውስጥ መሳሪያ አምራቾች ግብይት የተፈጸመበት መሆኑን አር ቲ ዘግቧል።
ብሪታንያ 68 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ሩሲያ 65 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ለወታደራዊ ግንባታ ወጪ በማድረግ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.