ህብረቱ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት የቀረበውን ሀሳብ እንደሚቀበለው አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት ያቀረቡትን ሀሳብ በደስታ እንደሚቀበለው አስታወቋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፥ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለማስተካከል ከቀጠናው የተውጣጣ ወታደራዊ ሀይል በፍጥነት እንዲሰማራ የወሰኑትን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም መሪዎቹ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል እንዲሁም በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ያለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እያደረጉ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
በተጨማሪም የህብረቱ የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት በየካቲት ወር ባደረገው 10ኛው የቀጠናዊ ምልከታ ጉባኤ የአፍሪካ ህብረት በሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያደረጋቸውን የስምምነት ማዕቀፎች ተግባራዊ እንዲደረጉ የአፍሪካ ህብረት እገዛ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቀደም ሲል የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በኬንያ ተገናኝተው በዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ አሸባሪዎችን ለመከላከል በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሀይል ለማስፈር መስማማታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!