Fana: At a Speed of Life!

የ ”ፊቼ ጫምባላላ” በዓል መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በሐዋሳ ከተማ መከበር ጀመረ፡፡
መርሐ ግብሩ በአባቶች ምርቃት መጀመሩን እና በሆሬ፣ በፋሮ፣ በቄጣላ በፈረስ ጉግስ እንዲሁም በሌሎች ባሕላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ መሆኑን የሲዳማ ክልል ፕሬስ ሴክሪታሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊሊፖስ ናሆም ገልፀዋል::
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በዓሉ የሰላም የመተባበር፣ የመተጋገዝ፣ የአንድነት በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሲዳማ ክልል ሆኖ በተዋቀረበት የ ”ፊቼ ጫምባላላ” በዓልን በማክበራቸው መደሰታቸውን ጠቅሰው÷ የፊቼ ጫምባላላን በዓል ለማክበር በሀዋሳ ለተገኙ እንግዶችም የእንኳ ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና እንግዶችም በበዓሉ ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።
የ ”ፊቼ ጫምባላላ” በዓል በዓለም የትምህርት፣ የሣይንስ እና ባሕል ድርጅት ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች በ2008 ዓ.ም መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.