Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የማምረቻ ኢንዱስትሪን ለመደገፍ የብሪታኒያ ኤምባሲ አብሮ እንደሚሰራ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የማምረቻ ኢንዱስትሪን ለመደገፍ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር አብሮ እንደሚሰራ የብሪታኒያ ኤምባሲ ገለጸ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የኤምባሲው የልማት ዳይሬክተር ፓውል ዋተርስ የማምረቻ ኢንዱስትሪን መደገፍ በሚቻልበት ጉዳይ እና በ”ኢትዮጵያ ታምርት” አገራዊ ንቅናቄ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፉ መንግስት የጀመራቸውን ጥረቶች ለመደገፍ እንደሚሰሩ የልማት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በተለይም የማምረቻ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለመደገፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማበረታታት፣ በቀጣይም በተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ይሰራልም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም እየተካሄደ ያለውን ኢትዮጵያ ታምርት አገራዊ ንቅናቄ በመደገፍ አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳለቸው አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ሀገራዊ ንቅናቄውን ለማሳካት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እራሱን የቻለ ቡድን ተቋቁሞ ስራዎች በጋራ ይሰራሉ ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.