የዓለም የሠራተኞች ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለ47ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።
የሠራተኞች ቀን “ሜይዴይ” የዓለም ሠራተኞች ለዘመናት ያካሄዱትን ታሪካዊ ትግል፣ ሠራተኞችና ንቅናቄዎቻቸው ያስገኟቸው ድሎች፣ የከፈሏቸው መስዋትነቶች በጋራ የሚዘክሩበትና የወደፊት ትልማቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው።
በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ድርጅቶች የተውጣጡ ሠራተኞች ቀኑን በአዲስ አበባ ስታዲየም እያከበሩ ይገኛሉ።
ሠራተኞቹ መንግስት የኑሮ ውድነቱን እንዲያሻሽል፣ የሠራተኞች የደሞዝ ወለል ማሻሻያ እንዲደረግበት፣ ሰላምን በማስከበር ሠራተኛው ሠርቶ መግባት እንዲችልና ሌሎችም የመብት ጥያቄዎችን አንስተዋል።
በነገው እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀኑ የሚከበር ይሆናል።
በዘመን በየነ