Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት የቴሌኮም ምርት እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ለማከፋፈል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ።
ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ኢትዮጵያ በ509 የራሱ የሽያጭ ማዕከል እንዲሁም በ134 የወኪል ሽያጭ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ምርትና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና የደንበኞችን አገልግሎት ለመጨመር ያስችለው ዘንድ÷ ዛሬ በብቸኛ አጋርነት እና ዋና አከፋፋይ በመሆን ከሚሰሩ ሰባት ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር ስምምነት መፈፀማቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልፀዋል።
እነዚህ ሀገር አቀፍ አከፋፋዮች ኢትዮ ቴሌኮምን በመወከል የቴሌብር አገልግሎት፣ የሞባይል ሲምካርድ እና የአየር ሰአት እንዲሁም የምትክ ሲም ካርድ አገልግሎት በዋና አከፋፋይነት እንዲሰሩ የወኪል ሽያጭ ማዕከል በመክፈት የኩባንያውን ምርት እና አገልግሎት ለደንበኞች እንዲሰጡ ያስችላቸዋልም ነው የተባለው፡፡
በቅድስት ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.