Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚን ጦር ያሸነፈችበትን የድል ቀን አከበረች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመን እና አጋሮቹን ያሸነፈችበትን 77ኛ አመት የድል ቀን አከበረች፡፡
የድል ቀኑን ለማክበር በሺዎች የሚቆጠሩ የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ዘመናዊ ታንኮች ፣ እንዲሁም የታጠቁ ተሽከርካሪዎች በሞስኮ ቀይ አደባባይ ትርዒት አሳይተዋል።
ዘመናዊው ቲ-14 የጦር ታንክ፣ ኤስ-400 የአየር መከላከያ ሚሳኤሎች እና ሌሎች ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የጦር መሳሪያዎች የድል ቀኑን አድምቀዋል።
ዝግጅቱን ተከትሎ ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሩሲያ ናዚዎችን ድል ስታደርግ በጦርነቱ ውስጥ የተዋጉትን ዘመዶቻቸውን የሚያሳይ ምስል ይዘው በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን አር ቲ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ ቀዩ አደባባይ ባሰሙት ንግግር፥ የሩሲያ ሰራዊት አባላት ዩክሬን ውስጥ “ለእናት ሀገራቸው ሰላምና ደህንነት መከበር ” እያደረጉ ያሉትን ውጊያ ያደነቁ ሲሆን፥ ሰራዊቱ በተለይ በዶምባስ ግዛት በጀግንነት እየተፋለመ መሆኑን ገልጸዋል።
የምዕረብ ሀገራት አገራችንን ለመውረር ዕቅድ አላቸው ሲሉም ተናግረዋል።
ምዕራባውያን ምድራችንን ለመውረር በመዘጋጀት ላይ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የምዕራባውያንን ወረራ ለማስቆም መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን በተጨማሪም የኔቶ ወታደራዊ ጥምረት በሩሲያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ስጋትን ፈጥሯልም ብለዋል፡፡
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ ላይ ሩሲያ ከዋሺንግተን ጋር በፀጥታ ዙሪያ ለመነጋገር ሙከራ አድርጋ እንደነበር እና የዘላቂ ሰላም ውይይቱም ፍሬ አልባ እንደነበር ፕሬዚዳንቱ አመላክተዋል፡፡
ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሩሲያውያን “በናዚዎች ላይ ያገኙትን ድል በእኛ አገር ላይ እንዲደግሙ አንፈቅድላቸውም” ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.