Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል በወንጀል መከላከል ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መንግስት እና በቱርክ መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
በፍትህ እና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ትብብሮች አስፈላጊና ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ ከብዙ አገራት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደምትሰራ የገለጹት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው፥ ከቱርክ መንግስት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረገው የጋራ ስምምነትም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቱርክ የኢትዮጵያ አጋር መሆኗን፣ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራጽ ዝግጁ መሆኗን፣ ቱርክ በሽብርተኛ ቡድኖች የደረሰባትን አሳዛኝ ጉዳቶች ኢትዮጵያ እንደምትገነዘብ እና ሽብርተኞችን እንደምታወግዝ እንዲሁም ሽብርተኝነት እንዳይስፋፋ ጠንክራ እንደምትሰራም ገልጸዋል፡፡
የቱርክ መንግስት የፍትህ ምክትል ሚኒስትር ያኩፕ ሞጉል በበኩላቸው÷ በቱርክና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል የተለያዩ ትብብሮች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ የፍትህ ትብብሮች ሰነድ መፈረማቸው ግንኙነቱን የበለጠ ሕጋዊ መሰረት የሚሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የሚፈለጉ ወንጀለኞችም በማንኛዉም ጊዜ በፍጥነት ተላልፈው መሰጠት አለባቸው ማለታቸውን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.