Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው በዘመናዊ ግብርና ሥራ ተሰማሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በማህበር በመደራጀት በዘመናዊ ግብርና ሥራ መሰማራታቸውን የጅማ ዞን አስታወቀ፡፡
የዞኑ የሙያና የስራ እድል ፈጠራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ለወጣቶቹ በ 111 ሚሊየን ብር የተገዙ 42 ትራክተሮች በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ተሰጥቷቸዋል።
በኦሞ ናዳ ክላስተር ተደራጅተው በስንዴና በቆሎ ምርት ላይ ለተሰማሩ 96 ወጣቶች 5 ትራክተሮችን በማስረከብ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡
ባለፉት 9 ወራት በዞኑ በግብርና እና በሌሎች የሥራ መስኮች 98 ሺህ 500 ሥራ አጦችን ከ8 ሺህ በላይ በሆኑ ማህበራት በማደራጀት እና የ190 ሚሊየን ብር ብድርና የስራ ቦታ በማመቻቸት የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡
በሁሴን ከማል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.