Fana: At a Speed of Life!

ኢዜአ ያሰባሰበውን ከ5ሺህ በላይ መፅሐፍት ለአብርሆት ቤተ- መጻሕፍት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ከተቋሙ ሠራተኞችና ከሌሎች አካላት ያሰባሰበውን ከ5ሺህ በላይ መፅሐፍት ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት አስረከበ።

ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት “ሚሊዮን መፅሐፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል መሪ ኃሳብ ለአንድ ወር የሚቆይ መፅሐፍትን የማሰባሰብ ጥሪ ተከትሎ በርካታ ተቋማትና ግለሰቦች ምላሽ እየሰጡ ነው።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በዛሬው ዕለት ከተቋሙ ሠራተኞችና ከሌሎች አካላት ያሰባሰበውን ከ5ሺህ በላይ መፅሐፍት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አስረክቧል።

መፅሐፍቱን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስረክበዋል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሠይፈ ደርቤ የተሰበሰቡት መፅሐፍት አንባቢው በብዙ የሚያተርፍባቸው እንደሆኑ ተናግረው ኢዜአ በቀጣይ ሁለተኛው ዙር የመፅሐፍት ማሰባሰብ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.