Fana: At a Speed of Life!

አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት እንዲጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ እንዲጠናከር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የፌዴራል እና የክልል የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችና ዳኞች የተሳተፉበት መድረክ በመንግሥታት ግንኙነት አዋጅ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የመንግስታት ግንኙነት አግባብነት፣ አስፈላጊነትና ጠቀሜታን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ ወደ ተግባር ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን÷ በተለይ የህግ ተርጓሚ አካላት ለፍትህ መስፈን እና ለዳኝነት ነፃነት መጎልበት በጎ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የግንኙነት መድረኩ እንዲጠናከር ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል።

በመድረኩ በቀረበው የውይይት ሰነድ ላይ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.