Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ክልሎች ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡
የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት እንደገለጹት÷ በክልሉ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና በ198 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀምሯል፡፡
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንዳመላከተው÷ 20 ሺህ 196 የቀንና የማታ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል፡፡
በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ188 ትምህርት ቤቶች 15 ሺህ 412 የሚሆኑ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እየወሰዱ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ጃፈር ሃሩን ገልጸዋል፡፡
ፈተናው በሁሉም ዞኖች እንደሚሰጥ ገልጸው÷ ሙሉ በሙሉ ሰላም ባልተረጋገጠባቸው አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ፈተና የማይወስዱ ተማሪዎች በቀጣይ የማካካሻ ትምህርት ወስደው በአጭር ወራት ውስጥ እንደሚፈተኑ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.