Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ በጎርፍ አደጋ የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ጥሪ አቀረቡ።

በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ መስጠት ተጀምሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በላሬ ወረዳ ተገኝተው እንዳሉት ፥ በክልሉ በስምንት ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ በርካታ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የክልሉ መንግስት ለአስቸኳይ ድጋፍ የሚሆን 10 ሚሊየን ብር መመደቡን ጠቅሰው ፥ ከደረሰው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

በስምንቱ ወረዳዎች ከ75 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ለተፈናቃዮች ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

በመሆኑም የደረሰውን ጉዳት ለመሸፈን ከክልሉ አቅም በላይ ስለሆነ ሁሉም አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.