Fana: At a Speed of Life!

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ የመከላከያ ዜዴዎችን ተግባራዊ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዩኒቨርሲቲዎች ውጭ በመላ ሀገሪቱ ትምህርት መቋረጡን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል።

ወደ ተግባር የገባው ኮሚቴ በቀጣይ ቀናት የግንዛቤ መፍጠርና የእጅ መታጠብ ዘመቻ ያካሂዳል።

በዚህም በተማሪዎቹ ማደሪያ ክፍሎች በር አስታጣቢ ተማሪዎችና ሰራተኞች ውሃ እና ሳሙና ይዘው ተማሪዎችን ያስታጥባሉ፣ የመከላከያ መንገዶችንም ያስተምራሉ ነው የተባለው።

እንዲሁም ወደ ግቢው የሚገቡ እንግዶች መግብያ በር ላይ ታጥበው እንዲገቡ ይደረጋልም ነው ያለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.