Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ህዝብ በህወሓት ምክንያት በስቃይ ላይ እንደሚገኝ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ህዝብ በህወሓት ምክንያት በችግር እና ስቃይ ላይ እንደሚገኝ በጥምር ጦሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች ተናገሩ።

በማይጠምሪ ግንባር የሽብር ቡድኑ ያሰለፋቸው ታጣቂዎች በጥምር ጦሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እነዚህ በቁጥጥር የዋሉ ታጣቂዎች፥ ህወሓት የትግራይ ህዝብን “ተከበሃል፣ ተወረሃል፤ ሁሉም ለጦርነት ይውጣ” በሚል ከየቤቱ አንድ አንድ ሰው እየወሰደ በግዳጅ በጦርነት ሲማግድ መቆየቱን ነው የተናገሩት።

በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከ6ኛ ክፍል በላይ የሆነን ሁሉ ወደ ጦርነት በመውሰድ ክልሉን ትውልድ አልባ እንዲሆን አድርጓልም ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት የክልል ህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቱን ተናግረው፥ ለጦርነት በግድ የገባው ወጣት ደግሞ በዱር በበረሃው እያለቀ ነው ብለዋል።

የህወሃት የሽብር ቡድን በማይጠምሪ ግንባር ያሰለፈው ክፍለ ጦር በጥምር ጦሩ ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበትም እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በጥምር ጦሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚህ ታጣቂዎች በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊው ክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.