Fana: At a Speed of Life!

ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው አካባቢዎች ርቀትን የመጠበቅ አስፈላጊነት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህክምና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እጅ መታጠብን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ።

ከዚህ ውስጥ ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ርቀትን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ነው የሚመክሩት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከማንኛው ሰው በ1 ነጥብ 8 ሜትር ራስን ማራቅ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ርቀትን የመጠበቁ ዋና አላማ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እና ለዓለም አቀፉ የጤና ስርዓት ድጋፍ ለሚፈልጉት ተጨማሪ ጊዜን ለመስጠት ነው ተብሏል።
ሆኖም በአዲስ አበባ በፋርማሲዎች አካባቢ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ተሰልፈው ታይተዋል።

በመሆኑም ስርጭቱን ለመቀነስ እና በቫይረሱ ላለመያዝ አጠገብዎ ካለው ሰው ሊኖርዎት የሚገባውን ርቀት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል መልዕክታችን ነው።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ዳቦ ቤትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲሁም በታክሲ እና አውቶብስ ፌርማታዎች ላይ መሰል ሰልፎችን እና መጠጋጋቶችን ማስወገድም ይገባል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.