Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለመከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ለ3ኛ ዙር ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊና የሎጅስቲክስ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለመከላከያ ሚኒስቴር ፋይናንስ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ዘላለም ፈተና አስረክበዋል፡፡
 
ድጋፉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍ የምግብ ቁሳቁስ፣ ሰንጋዎች እና በጎችን እንዲሁም የንጽህና መጠበቂያ እና መገልገያ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በሳሙኤል ወርቅአየሁ
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.