Fana: At a Speed of Life!

የደመራ በዓል በሚከበርበት የመስቀል አደባባይ የጽዳት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የደመራ በዓል ምክንያት በማድረግ በዓሉ የሚካሄድበትን ቦታ የማፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በፅዳት ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የተለያዩ እምነት ተከታይ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የፅዳት ዘመቻው የተለያዩ እምነት ተከታዮች አብሮነታቸውን ለማሳየት እና መልካም ምኞታቸውን እንዲገልፁ ታስቦ መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከጽዳት ዘመቻው በኋላ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሬት ጽሑፍ÷ የመስቀል ደመራ በዓል በሚከበርበት የመስቀል አደባባይ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎችና ምዕመናን የተሳተፉበት፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን የገለጹበት የፅዳት ዘመቻ መከናወኑንና ቦታው ለበዓሉ ዝግጁ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮጵያውያን÷ አንድነታችን የጥንካሬያችን መሰረት፣ መተሳሰባችን ያቆራኘን ኢትዮጵያዊነት ማሰሪያችን፣ መከባበራችን የአብሮ መኖራችን ምስጢርና መለያችን ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል ብለዋል፡፡

ትውልዱም ይህንን ድንቅ ጥበብና ምስጢር ይዞ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.