Fana: At a Speed of Life!

ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ15ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል ዛሬ ተመረቀ፡፡

ማዕከሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ አመራሮች በተገኙበት ነው ዛሬ የተመረቀው፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ዱጉማ ከህዝብ ብዛት መጨመር ከቴክኖሎጂዎች መስፋፋት እና ከአኗኗር ዘይቤአችን ጋር ተያይዞ ከዕለት ወደ ዕለት ድንገተኛ አደጋዎች መበራከታቸውን በመግለፅ በአሁኑ ጊዜ በ8 ከተሞች የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል ግንባታ ተግባራዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው፥ ማዕከሉ በአስተዳደሩ ለረጅም አመታት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በምሥራቁ የሀገሪቱ ክፍል ለሚከሰቱ አደጋዎች አፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጥና በየሆስፒታሎች ውስጥ ያለውን መጨናነቅ ይቀንሳልም ነው ያሉት፡፡

ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ማዕከሉ ለድሬዳዋ አስተዳደር እና ለአጎራባች ክልሎችና አካባቢዎች አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በቲያ ኑሬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.