በሶሪያ የኮሌራ በሽታ ተቀሰቀሰ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶሪያ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በተቀሰቀሰ የኮሌራ በሽታ 29 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተነገረ፡፡
እንደ ተመድ ጦርነት በጎዳት ሶሪያ የኮሌራ በሽታ መቀስቀሱ የሀገሪቷን ችግር ከድጡ ወደ ማጡ ያደርገዋል፡፡
በሶሪያ ካለፈው ወር ጀምሮ ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ወዲህ እስካሁን 338 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
የሶሪያ ሰሜናዊ አሊፖ ግዛት ደግሞ በርካታ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበበት ቦታ ነው፡፡
በሌላ በኩል በአፍሪካ ኡጋንዳ በኢቦላ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 መድረሱ ተነግሯል፡፡
ከ16ቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች የአራቱ ሰዎች ሕይወት አልፏል ነው የተባለው፡፡
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ኬንያ እና ታንዛኒያ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውም ተነግሯል፡፡