Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

መሪዎቹ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

በተለይም የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ እንዲሆን አብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ትኩረት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከአዲሱ የሶማሊያ አስተዳደር ጋር በተለያዩ ደረጃዎች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በተለይም ለኢኮኖሚ ዕድገት አጽንኦት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ጠንካራ እና የተረጋጋች ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ጥንካሬ የሚጠቅም መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ሶማሊያን ለማስቻል ለከፈሉት መስዋዕትነት አድናቆታቸውን ገልፀው፥ ሁለቱ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ችግሮች ለመፍታት የትብብር አስፈላጊነትን አመላክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.