Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉን የዋጋ ግሽበት ለመቋቋም ሥር-ነቀል የፖሊሲ ለውጥ ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለውን የዋጋ ግሽበት ለመቋቋም እና ዕድገት ለማስቀጠል ሥር-ነቀል የፖሊሲ ለውጦች እንደሚያስፈልጉ የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ ገለጹ፡፡

በዓለማችን እየተስተዋሉ ያሉ ተደራራቢ ቀውሶች ዓለማችንን ወደ ኢኮኖሚያዊ ድቀት እየመሯት መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ዓለማችን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መቀስቀስ ምክንያት ለምግብ ዋጋ መናር፣ ለኑሮ ውድነት እና ለኃይል አቅርቦት ችግር ተጋልጣለች፡፡

ከዚህ ባለፈም በሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት የተባባሰው የምግብ ዋጋ መናር ለዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ድቀት ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ትልቁን ስፍራ መያዛቸውን ኃላፊው በጄኔቫ በተሰናዳው የዓለም አቀፉ ንግድ ድርጅት ዓመታዊ የህዝብ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የዕድገት ትንበያ የዓለም ዕድገት መገታቱንና መጥፎ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

አሁን ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሰብ እና የዓለማችንን ዕድገት ወደ ቀድሞው መመለስ እንደሚገባው ኦኮንጆ-ኢዌላ መግለጻቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.