Fana: At a Speed of Life!

የየም ቋንቋን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ የፖናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የየም ቋንቋን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ምሁራን ጋር የፖናል ውይይት ተካሄደ።

በየም ልዩ ወረዳ ሳጃ ከተማ በተካሄደው የፓናል ውይይት “የምሳ” የተሰኘውን የብሔረሰቡን ቋንቋ ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ከሆኑት ዶክታር ለማ ንጋቱ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቧል፡፡

የየም ብሔረሰብ ቋንቋውን ከአፍ መፍቻነት በተጨማሪ ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር መጠቀም እንደሚኖርበት ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት፡፡

የየም ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሳሙዔል ገብረ ሚካኤል የልዩ ወረዳው ኅብረተሰብ በታማኝነቱና ሥራ ወዳድነቱ እንደሚታወቅ ገልጸው ቋንቋውን ለማሳደግም በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በተመስገን አለባቸው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.