Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ደርሶባቸው በ150 ሚሊየን ብር የተገነቡ ተቋማት እየተመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ውድመት በደረሰባቸው ሰባት ከተሞች በ150 ሚሊየን ብር የተገነቡ የትምህርት ቤቶችና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እየተመረቁ ነው፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በምርቃ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ጦርነቱ  ከፍተኛ ውድመት በአካባቢው ላይ ያደረሰ ቢሆንም በቁጭት በመነሳት የተሻሉና ጥራታቸው ከፍ ያሉ የትምህርትና የጤና ተቋማትን ገንብተናል ብለዋል፡፡

ዛሬ በኮምቦልቻ እና ከሚሴ ከተሞች የተመረቁት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እና ትምህርት ቤቶች 30 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነ   በበኩላቸው÷ በአማራ ክልል 228 ከተሞች በአሸባሪው ህወሐት ወረራ የመሰረተ ልማት ውድመት የደረሰባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሸዋሮቢት፣  ከሚሴ፣  ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣  ላሊበላ እና ሰቆጣ ከተሞች የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆናቸውንም ሃላፊው  ጠቁመዋል፡፡

 

በኢሳያስ ገላው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.