Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ 10 ሚሊየን ኩንታል በበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 10 ሚሊየን ኩንታል በበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው እንደገለፁት÷ በዘንድሮው ዓመት የበጋ መስኖ የተሻለ የስንዴ ምርት ለማምረት በሁሉም ግብርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ።
በ2014 የበጋ መስኖ ልማት በክልሉ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የስንዴ ምርት የተገኘ ሲሆን÷ይህን ልምድ የበለጠ በማሻሻል በዘንድሮው የበጋ መስኖ 250 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
በባለፈው በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንደ ክልል በሄክታር 36 ኩንታል ስንዴ ማምረት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
በተያዘው ዓመት በሄክታር 40 ኩንታል ስንዴ ለማምረት ግብ መቀመጡንም ምክትል ሃላፊው ተናግረዋል ።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.