Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን  የተለያዩ ሹመቶች አጽድቋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

  1. ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

 

  1. አቶ ምትኩ አስማረ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

 

  1. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

 

  1. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ፡- የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ

 

  1. ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር

 

  1. አቶ ጀማል ረዲ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተሾመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትንና የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑትን የወይዘሮ ሀቢባ ዑመርን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.