Fana: At a Speed of Life!

ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ጠየቁ።

የሀገር አቀፍ፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሕግ አውጭዎች የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳን የሕዝብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ይህም ሕዝቡ ፋይዳው ለራሱ መሆኑን አውቆ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ያግዛል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሀገራዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቁ ጠቅሰው÷ የሕግ አውጭዎች ኃላፊነት ጉልህ መሆን እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፥ ለሀገራዊ ምክክር መሳካት የሁሉም ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት ኮሚሽኑ ያለምንም የውጭና የውስጥ ጣልቃ ገብነት የተሰጠውን ኃላፊነት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ እያከናወኗቸው ባሉ ተግባራት ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በሙክታር ጣሃ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.