Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ ከሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አቶ ሙስጠፌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲና ልዑካናቸው በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት እና የሰላም ስራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ልዑካኑ በጅግጅጋ ከተማ በፌዴራል እና በክልሉ መንግሥት የተሰሩ እና በመገንባት ላይ የሚገኙ በርካታ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን  መጎብኘታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ እና ልዑካቸው በባህርዳር ከተማ በተካሄደው 10ኛው የጣና ፎረም መሳተፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.