Fana: At a Speed of Life!

በክልሎች ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ በቀረበ ሠነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች ”በደም የተከበረ በላብ የታሰረ” በሚል መሪ ሐሳብ ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ዕድገት የማረጋገጥ ውጥኖች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

እስካሁን ድረስ በጋምቤላ እና ሐረሪ ክልሎች ውይይቱ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ በሶማሌ ክልል እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደግሞ በመካሄድ ላይ ነው፡፡፡

በጋምቤላ ክልል በተካሄደው መድረክ፥ በጫና ሳይበገር ሉዓላዊነትን ያጠናከረ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ ከአረንጓዴ ዐሻራ ወደ ሌማት ትሩፋት እንዲሁም የፖለቲካ ዕድገት ጉዞ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በተመሳሳይ በሐረሪ ክልል በተካሄደው መድረክ÷ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከሚከፈለው የደም መስዋዕትነት ባሻገር ቀጣይነት ያለው ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማረጋገጥ የሀገር ክብር እና ነፃነት በላባችን እንዲጸና ማድረግ ይገባል ተብሏል፡፡

የችግሮችን ምንጭ በመለየት እና በመረባረብ በላብ የታሠረ ተግባር በመፈጸም ጠንካራ ኢኮኖሚ በመገንባት በየደረጃው ራስን በምግብ መቻል እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

አመራሩ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም በሶማሌ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ፥ ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ዕድገት የማረጋገጥ ውጥኖችን በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ÷ ሀገራዊ ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ ብሎም ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን የዳሰሰውና ለውይይት የቀረበው ሠነድ የአመራሩን የመፈጸም አቅም እንደሚያሳድግ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.