Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን አስታወቀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው እንደተናገሩት÷ ባንኩ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከዚህ ቀደም ከሰጠው ብድር ውስጥ 4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ማስመለስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር 65 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ በሩብ ዓመቱ 4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብድር ያፀደቀ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህም ውስጥ የአምራች ዘርፉ ከፍተኛውን የብድር ድርሻ እንደሚይዝ ተናግረዋል፡፡

ባንኩ በሩብ ዓመቱ ለመስጠት ካጸደቀው የብድር መጠን ውስጥ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚሆኑን መስጠቱን ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ አገልግሎቱን ቀልጣፋ ማድረጉና ተበዳሪዎች ውጤታማ ስራ ማከናወን እንዲችሉ ስልጠና መስጠቱ ለአፈፃፀሙ መሻሻል አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል።

ባንኩ በሩብ አመቱ 740 ሚሊየን ብር ትርፍ እንዳገኘ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.