Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገር ኢኮኖሚ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ – አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገር ኢኮኖሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችል አቅም እንዳላቸው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡

አቶ ርስቱ ይርዳ በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ በ79 ሄክታር መሬት ላይ በወጣቶች እየለማ  የሚገኝ የጤፍ ሰብልን ጎብኝተዋል።፡፡

በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት ፥ ወጣቶች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው በሀገር ኢኮኖሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችል አቅም አላቸው ።

በዚህ ተጠቃሚ እየሆኑ ከሚገኙ ወጣቶች መካከልም ሲሉ አዲሱ በለጠ አንዱ ነው፡፡

በጋራ በመሆን በሁምቦ በ3 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ጤፍ እያለሙ የሚገኙት ወጣቶች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን አንስተዋል።

ወጣቶች ጊዜና ጉልበታቸውን በአግባቡ በመጠቀም በተገኘው የስራ አማራጭ ከራሳቸው አልፈው ሀገርንና ህዝብን ማገልገል ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

በወላይታ ዞን በ1 ሺህ 50 ሄክታር መሬት ላይ 2 ሺህ 700 ወጣቶች በልዩ ልዩ የግብርና ስራዎች ተደራጅተው እየሰሩ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.