Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ትርኢት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ትርኢት ከጥቅምት 25 እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና የፋሽን ዓለም አቀፍ መድረክ ዓለም አቀፍ የጨርቃጨርቅ አምራቾችና ላኪዎች የሚያገናኝ መድረክ ነው።

የንግድ ትርኢቱ በአፍሪካ የጥጥ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የአልባሳት፣ የቆዳና የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በንግድ ትርኢቱ ላይ ከ200 በላይ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ አምራቾችና ላኪዎች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ የንግድ ትርኢቱ ለአፍሪካውያን አምራቾች የእርስ በእርስ ትስስር ለመፍጠርም ያለመ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

የንግድ ትርኢቱ የአፍሪካን ነፃ አህጉራዊ ንግድ የሚያመቻች መሆኑም ነው የተመለከተው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር ከመሴ ፍራንክፈርት ኢግዚቪሽን ጋር በመተባበር መድረኩን አዘጋጅተውታል።

በፋሽን ሳምንቱ ፋሽን ሾው፣ ውይይት እና የልምድ ልውውጥ መድረክ እንደሚኖር ይጠበቃል።

በትእግስት ብርሃኔ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.