Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ድሮን እና ታንክን ጨምሮ ለዩክሬን የምታደርገውን የ400 ሚሊየን ዩሮ ወታደራዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ድሮን እና ታንክን ጨምሮ ለዩክሬን የምታደርገውን የ400 ሚሊየን ዩሮ የወታደራዊ ድጋፍ ፓኬጅ ይፋ አድርጋለች።

የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት የቆዩና የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ትጠቀምባቸው የነበሩ ታንኮች፣ ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች እና ካሚካዝ ድሮኖችን በአዲሱ ወታደራዊ ድጋፉ ማካተቱን አስታውቋል።

የአሁኑ ወታደራዊ ድጋፍ ፔንታገን ለዩክሬን በሚያደርገው የ3 ቢሊየን ዶላር የደህንነት ድጋፍ ውስጥ የሚካተት መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሜሪካ መሳሪያዎቹን ከአቅራቢዎችና ሻጮች ላይ በመግዛት ለዩክሬን ቀጥታ የምታቀርብ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

በዚህ መሰረትም 45 እንደገና ተሻሽለው የተሰሩ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ስሪት የሆኑ ቲ 72 ታንኮች፣ ሃውክ ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤል፣ 250 መሳሪያ የታጠቁ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ 40 የጦር መሳሪያ የታጠቁ ጀልባዎች እንዲሁም 1 ሺህ 100 ድሮኖችን ዩክሬን ታገኛለች ተብሏል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.