Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ማስተር ፕላን ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሚቀጥሉት 30 አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ብሔራዊ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ማስተር ፕላን ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ማስተር ፕላኑ የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን የሀገር ኢኮኖሚን ለማሳደግ ታስቦ የተጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ማስተር ፕላኑ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር የሚያደርግ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

ትራንስፖርትን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ግብርና፣ ማምረቻ ዘርፍ፣ ማዕድን እና ቱሪዝም ዘርፎች እንዲያድጉ እንደሚያግዝም አስረድተዋል።

ይፋ የተደረገው የተቀናጀ የትራንስፖርትና የሎጂስትክ ማስተር ፕላን የመንገድ ተደራሽነትንና ጥራትን የሚያሳድግ ስለመሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።

ብሔራዊ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ማስተር ፕላን ከየብስ ባለፈ ለአየር ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ልዩ ትኩረት የሰጠ እንደሆነም ተገልጿል።

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.