Fana: At a Speed of Life!

በታንዛኒያ እስር ላይ የነበሩ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ በታንዛኒያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለእስር ተዳርገው የነበሩ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ የቻሉት÷ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በሀገሪቱ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ጋር በቅንጅት በሠሩት ሥራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይም ዜጎች በህገ-ወጥ ደላላዎች አማካኝነት ከሚደረግ መሰል አደገኛ ጉዞ እንዲታቀቡ ኤምባሲው ጥሪ አቀርቧል፡፡

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም ድርጊቱን ከምንጩ ለማድረቅ በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.