Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራት አባል እንዲሆን ድጋፏን እንደምትሰጥ ቻይና ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራት ስብስብን ቢቀላቀል ቻይና እንደምትደግፍ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ሺ ይህን የሀገራቸውን አቋም ኢንዶኔዥያ በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ አስታውቀዋል።

የቡድን 20 ስብስብ የዓለማችንን ግንባር ቀደም በኢኮኖሚ የጠነከሩ ሀገራትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፥ የአውሮፓ ህብረትም የዚህ ስብስብ ቋሚ አባል ነው።

ስብስቡ የዓለምን 60 በመቶ ህዝብ፣ 80 በመቶ ኢኮኖሚ እና 75 በመቶ የወጪ ንግድን የሚሸፍን ነው።

ነገር ግን በቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ብቸኛዋ ከአፍሪካ የተወከለች ሀገር ናት።

በኢንዶኔዥያው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የቡድን 20 አባል ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን በቋሚ አባልነት እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበው ነበር።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.