Fana: At a Speed of Life!

ካሪም ቤንዜማ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጪ መሆኑን ብሔራዊ ቡድኑ አስታውቋል፡፡

ካሪም ቤንዜማ ከውድድሩ ውጭ የሆነው በትናንትናው ዕለት በልምምድ ላይ ሳለ ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት መሆኑን የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

የ2022 የባሎንዶር አሸናፊው ቤንዜማ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ቢያንስ ሦስት ሳምንታት እንደሚያስፈልገው ተዘግቧል፡፡

የቤንዜማ ከውድድሩ ውጪ መሆን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ጉዳት መሆኑም ተገልጿል፡፡

በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ማምሻውን በኳታር ይጀመራል።

የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱን ተከትሎ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኳታር ከኢኳዶር የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.